የኛ ክለብ
=========
ክለባችን ከተመሰረተ ቆየ፡፡ ክለሰቡ ሰፊ ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በውስጡ አሉ፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ክለባቻን ሰላም አጥቶ ቆየ፡፡ የክለባችን ኃላፊ አቶ ዕከ በዚህ ዙሪያ ሰላም ለመፍጣር እየጣሩ ነበር፡፡ የክለቡ አባላት ተቃወሙ፣ስራ አቆሙ፣ንብረት ሰበሩ፡፡ በዚህም ክለባችን ከጨዋታ ለመወገድ ተገደደ፡፡ በመጨረሻ ግን ኃላፊው ትልቅ ስብሰባ አካሄደው ውይይት ተደረገ፡፡ የክለቡ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡ አንዳንደች ‹‹እንደ አንድ ክለብ ማሰብ ተስኖናል›› ሲሉ ሌሎቸ ደግሞ ‹‹ተከፋፍለናል›› ሲሉ ጮኩ፡፡ በክለቡ ውስጥ መድሎ፣ መከፋፈል፣ዘረኝነት ወዘተ እንዳለ ተገለጸ፡፡ ለዚህ ደግሞ አሁን ያለው አመራር መቀየር እንዳለበት የክለቡ አባላት ወተወቱ፡፡ በዚህ የተነሳም አዲስ የክለቡ መሪ ምርጫ እንደሚካሄድ ተወሰነ፡፡ ያኔ የክለቡ አባላት ተደሰቱ፣ጨፈሩ፡፡
ቀኑ ደረሰና አዲስ መሪ ተመርጦ ይፋ ሲደረግ የክለባችን ሰዎች በሙሉ ጨፈሩ፡፡ ተገባበዝን፣አብረን በላን፣ጠጣን፡፡  በቃ በክለቡ ውስጥ ለውጥ በአንዴ እንደሚመጣ አመንንና ተስፋ አደረግን፡፡
አዲሱ መሪ ከተመረጡ ቀናት፣ወራት አለፉ፡፡ ቀስ በቀስ ግን አሁንም አዲሴ የክለባችን መሪ ላይ ሃሜቶች መሰማት ጀመሩ፡፡ አንዳንዶች ‹‹አዲሱ የክለባችን መሪ የድሮው መሪዎች ቀኝ እጅ ናቸው›› ሲሉ ፌስ ቡክ ላይ ጻፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የክለቡ የበላይ ጠባቂ በጣም መበሳሰጨት ጀመሩ፡፡ ወዲያውን ስብሰባ ጠሩና መራር የሆነ ንግግር ተናገሩ፡፡ እንዲህ ሲሉ በነገር ሸነቆጡን፡፡

‹‹አሁን አሁን የእናንተ ነገር እየከበደኝ ነው፡፡ ለመሆኑ ዋናው ጥያቄያችሁ ምን ነበር? የመሪ ለውጥ ብናደርግም እናንተ ግን አልተለወጣችሁም፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ እናንተ ካልተለወጣችሁ መሪውም አይለወጥም፡፡ ሁልጊዜ የምታስቡት ከተደረገላችሁ ይልቅ ያልተደረገላችሁን ነው፡፡ ባላችሁ ነገር እንኳ አታመሰግኑም፡፡ ምን ቢደረግላችሁ ይሆን የምትደሰቱት? ዛሬም በክለቡ ውስጥ ዘር ትቆጥራላችሁ፡፡ እኔ ምን ሰራሁ? ብላችሁ አትጠይቁም፡፡ ሳስበው በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን ክለባችን ሰላም አይኖረውም፡፡ ሀበሻ ስንባል ከምቀኝነት ያለፈ ስራ የለንም፡፡ ወሬ ወዳጆች ነን፣ሃሜተኞች ነን፡፡ ራሳሳችንን ከመተቼት ይልቅ ሌሎችን መተቼት መለያችን ነው፡፡ ነገስ ሌላ መሪ ብንመርጥ ይህ ባህሪያችን ይቀየር ይሆን? ወይስ መሪ ከማርስ እናምጣ? ወይስ ፈጣሪ ይምጣና ያስተዳድረን? እውነቴን ነው የምላችሁ ሀበሻ ስንባል ፈጣሪ ምድር ላይ ወርዶ መሪ ቢሆን እንኳ ለመተቼት ወደኃላ አንልም? እና ምን ተሻላችሁ? ክለቡን እንበትነው? 

Comments